መደበኛ ያልሆነ

ህዳር 20፤2014-በጥቅምት ወር በተፈጸመ የባቡር ኬብል ስርቆት ከ1.4 ሚሊዮን ብር በላይ ኪሳራ መድረሱ ተገለጸ

በጥቅምት ወር በተፈጸመ የባቡር ኬብል ስርቆት ከ1.4 ሚሊዮን ብር በላይ ኪሳራ መድረሱ ተገለጸ

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በ2014 በጀት ዓመት ጥቅምት ወር በተፈፀም የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ግብዓት እና የኃይል ስርቆት ምክንያት ከ1 ሚሊዮን 437 ሺህ 967 ብር ጉዳት መድረሱን አስታዉቋል፡፡ በሌላ በኩል በአዲስ አበባ ቀላል ባቡር አገልግሎት በአንድ የባቡር መስመር ላይ 700 ሜትር የሚደርስ የባቡር ኬብል ላይ በተፈጸመ የስርቆት ወንጀል 1.4 ሚሊዮን ብር የገንዘብ ኪሳራ እንደደረሰ የአዲስ አበባ ከተማ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የኮሚኒኬሽን ክፍል ሃላፊ የሆኑት አቶ በቀለ ክፍሌ በተለይ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡

አያይዘውም በተለያዩ አካባቢዎች በተለይም ደግሞ በኮልፌ ቀራንዮ እየተስተዋለ የሚገኘዉ የሃይል መቆራረጥ እየተፈጠረ ያለው በትራንስፎርመር መቃጠል እና በኬብል መበላሸት ምክንያት መሆኑን ገልጸዋል፡ በእነዚህ አካባቢዎች ያሉትን ችግሮች ለመቅረፍ በከፍተኛ ደረጃ እየተሰራ ሲሆን አለም ባንክ ላይ ችግሩ መቀረፉን ኃላፊዉ ገልጸዋል፡፡

በአየር ጤና ለተከታታይ አምስት ቀናት ለተፈጠረው የአሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥ ትራንስፎርመር እየተቀየረ ስለሆነ በ24 ሰዓት ችግሩ እንደሚቀረፍ አቶ በቀለ ክፍሌ ጨምሮ ለብስራት ራዲዮ ተናግረዋል፡፡

በኤደን ሽመልስ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *