መደበኛ ያልሆነ

ህዳር 20፤2014-አመታዊው የአዳዲ እና የአብማ ማርያም ንግስ በአል በሰላም ለማክበር አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት መደረጉን ፖሊስ አስታወቀ❗️

አመታዊው የአዳዲ እና የአብማ ማርያም ንግስ በአል በሰላም ለማክበር አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት መደረጉን ፖሊስ አስታወቀ❗️

በደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር በየአመቱ በድምቀት ከሚከበሩ የሀይማኖት በአላት መካከል በጸርሐ ፅዮን አብማ ማርያም ካቴድራል ቤተክርስቲያን ህዳር 21 የሚከበረው የአብማ ማርያም ክብረ በአል አንዱ ነው፡፡

በዓሉን በሰላም ለማክበር ከፀጥታ ሀይሉ እና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ተደርጎ ስምሪት መሠጠቱንና ፖሊስ አስፈላጊ ቅድመ ዝግጅት ስለማድረጉ የ1ኛ ፖሊስ ጣቢያ ሀላፊ ምክትል ኮማንደር ጌትነት መስፍን ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡

ህብረተሰቡ በዓሉን በሚያከብርበት ግዜ አጠራጣሪ ሁኔታዎች እና ፀጉረ ልውጦች በሚያጋጥሙበት ግዜ በአካባቢው ለተመደቡ የጸጥታ ሀይሎች ጥቆማ በመስጠት እና የፖሊስ እርዳታ ሲያስፈልግ 058-77-11-6-69 በመደወል ጥቆማውን እንዲያደርስ ጥሪ ቀርቧል፡፡

በሌላ በኩል በኦሮሚያ ክልል ደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ቀርሳ መሊማ ወረዳ አዳዲ ከተማ ለሚከበረው አዳዲ ማርያም ክብረ በዓል ፣ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት ማደረጉን እንዳለበት የወረዳው ፖሊስ አዛዥ ዋና ኢንስፔክተር አበራ ታዬ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡
በክብረ በዓሉ ከ50 ሺ በላይ ሰዎች እንደሚገኙ እና ህብረተሰቡም አጠራጣሪ ነገር ሲመለከት በአካባቢው ለሚገኝ ፖሊስ ማሳወቅ እንደሚገባም ዋና ኢንስፔክተር አበራ ታዬ ጨምረው ለጣቢያችን ተናግረዋል፡፡

ሳምራዊት ስዩም

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *