መደበኛ ያልሆነ

ህዳር 20፤2014-ኢትዮጲያን ለማፍረስ ቆርጦ የተነሳው የሽብር ቡድን ሱዳንን መደበቂያው እንዳያደርግ እየሰራሁ ነው ሲል መንግስት አስታወቀ !!

የኢትዮጲያ መንግስት ከሰሞኑ የሱዳን ወታደሮች ላይ ጥቃት ሰነዘረ የሚለው መረጃ ከእውነታው የራቀ ነው ሲል መንግስት ያስታወቀ ሲሆን የተወሰደው እርምጃ በማህበረሰቡ ላይ ጉዳት ለማድረስ በመጣ አካል ላይ የተወሰደ መሆኑን የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስትር ድኤታ ወ/ሮ ሰለማዊት ካሳ ተናግረዋል ፡፡

በአሁን ሰዓት ሱዳን በወረራ ከያዘቻቸው ስፍራዎች በሰላማዊ መንገድ እንድትለቅ ለማድረግ መንግስት እየሰራ እንደሚገኝ ሚኒስትር ድኤታዋ በተያያዥነት ገልፀዋል ፡፡

ኢትዮጲያን ለማፍረስ ቆርጦ የተነሳው የሽብር ቡድን ሱዳን መደበቂያው እንዳትሆን ለማድረግ እየሰራ ይገኛል ሲሉ ወ/ሮ ሰለማዊት ተናግረዋል ፡፡

በአሁን ሰዓትም ኢትዮጲያ እና ሱዳን የነበራቸውን የረዥም ዘመናት ወዳጅነት ለማሻከር ይሁነኝ ብለው እየሰሩ እና እየተነቀሳቀሱ የሚገኙ አካላት ተሳሳቱ ዘገባዎችን እያሰራጩ ይገኛሉ ብለዋል ፡፡

በተጨማሪም በአሁን ሰዓት ሀገሪቱ እየተጋፈጠች የምትገኘው ሁለተኛው አውደ ውጊያ ተደርጎ የሚቆጠረው የኢኮኖሚ ዘረፍሩ እንዳይጎዳ ለማድረግ ስራዎች እየተሰሩ ነው ሲሉ ሚኒስትር ድኤታዋ በተጨማሪነት ተናረዋል ፡፡

ናትናኤል ሀብታሙ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *