መደበኛ ያልሆነ

ህዳር 20፤2014-ኢትዮጵያን ለማፍረስ የተነሳን ሀይል እንደሚፋለም ሻለቃ አትሌት ሀይሌ ገ/ስላሴ ተናገረ

ኢትዮጵያን ለማፍረስ የተነሳን ሀይል እንደሚፋለም ሻለቃ አትሌት ሀይሌ ገ/ስላሴ ተናገረ

ኢትዮጵያን ለማፍረስ ከሚነሳ የትኛውም ሀይልጋር እንደሚፋለም ሻለቃ አትሌት ሀይሌ ገ/ስላሴ ከስካይ ኒዉስ ጋር ባደረገዉ ቆይታ ተናግሯል ።

ከወንድም እና ከ እህቶቼ ጋር ችግር የለብኝም ነገር ግን ሀገሬን ለማፍረስ የሚፈልግ አካል ጋር ግን እፋለማለሁ ሲል አትሌቱ ለስካይ ኒዉስ በሰጠዉ ቃል ተናግሯል።

በተጨማሪም ወደ ጦርነት ገብተህ መሳሪያ ታነሳለህ ተብሎ ጥያቄ የቀረበለት አትሌቱ በፖሊስ ሰራዊት ውስጥ ሻለቃ ነኝ መሳሪያ ባነሳ እንዳይገርምህ ሲል ምላሹን ሰጥቷል።

ከኢትዮጵያ ጋር የረጅም አመታት ግንኙነት ያላቸዉ ሀገራት ኢትዮጵያ ችግር ዉስጥ በሆነችበት ወቅት ኢትዮጵያ ላይ እያደረጉ ያሉት ጫና እንላስዳስደተዉ እና ተገቢ እንዳልሆነ አትሌቱ ጨምሮ ለስካይ ኒዉስ ተናግሯል።

አትሌቱ በቅርቡ ኢትዮጵያ ከአሸባሪዉ ህወሓት ጋር እያካሄደች ያለዉን ጦርነት በግንባር ለመፋለም መዘጋጀቱን ማስታወቁ የሚታወስ ነዉ።

በበረከት ሞገስ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *