መደበኛ ያልሆነ

ህዳር 20፤2014-በኒጀር በኮሌራ የተነሳ የ156 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተሰማ

በኒጀር በኮሌራ የተነሳ የ156 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተሰማ

የዓለም የጤና ድርጅት በኒጀር ኮሌራ ወረርሽኝ መሆኑን ይፋ ካደረገ ከሶስት ወራት በኋላ በሀገሪቱ እስካሁን 156 ሰዎች በኮሌራ በሽታ መሞታቸውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታውቋል።በማራዲ ምስራቃዊ ክልል በአገር አቀፍ ደረጃ ከ5,400 በላይ ሰዎች በኮሌራ ተጠቅተዋል።

የማራዲ ክልል ከናይጄሪያ ጋር የሚዋሰን በመሆኑ ለናይጄሪያ ስጋት ፈጥሯል፡፡በነሀሴ ወር የዝናብ ወቅት እንደመሆኑ ከንፅህ መጠን ዉሃ አጠቃቀም ጋር የነበረ የንጽህና ጉድለት ለወረርሽኙ መስፋፋት ምክንያት ሆኗል፡፡

ወረርሽኙ ወደ ሌሎች የሀገሪቱ ክፍሎች እና ወደ ጎረቤት ሀገራት በተለይም በኒጀር፣ ቡርኪናፋሶ እና ማሊ መካከል ባለው የሶስት ድንበር አካባቢ ሊዛመት እንደሚችል ስጋት አሳድሯል፡፡

በሚኪያስ ፀጋዬ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *