መደበኛ ያልሆነ

ህዳር 21፤2014-በሞተር ሳይክል የጦር መሳሪያ ሲያጓጉዙ የነበሩት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ

በሞተር ሳይክል የጦር መሳሪያ ሲያጓጉዙ የነበሩት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ

በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ወረጃርሶ ወረዳ የሰሌዳ ቁጥሩ 78468 ኦሮ በሆነ የሞተር ሳይክል የጦር መሳሪያ ደብቀው ወደ ሌላ ቦታ ለማዘዋወር እና ኬላ ላይ ደብቆ ለማሳለፍ ሙከራ አድርገዋል። ሆኖም ግን ህብረተሰቡ አስቀድሞ በመጠራጠር ለፖሊስ በሰው ጥቆማ መሰረት በቁጥጥር ስር ማዋል ተችሏል፡፡

በፍተሻ ወቅት በርካታ የጦር መሳሪያዎች የተያዙ ሲሆን እነዚህም 978 የብሬል ጥይት ፤35 የክላሽንኮቭ ጥይት ፤45 የኢኮል ጥይት ተይዟል። በመሆኑም መሳሪያዎቹን ሲያዘዋውሩ የነበሩት ግለሰቦች እንዲሁም የሞተር ሳይክሉ አሽከርካሪ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የወረጃርሶ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት ምክትል ዳይሬክተር ኢንስፔክተር ታምሩ ባይሳ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።

በኤደን ሽመልስ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *