መደበኛ ያልሆነ

ህዳር 21፤2014-በኢትዮጲያ በወሲብ ንግድ ላይ ከተሰማሩ ከ210 ሺህ በላይ ሴቶች የኤች አይ ቪ ምርመራ ያደረጉት 59 በመቶ ብቻ መሆናቸው ተነገረ ❗️

በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ33ተኛ ጊዜ የሚከበረው የዓለም የኤድስ ቀን ህዳር 22 /2014 ዓ.ም በኢትዮጵያ ታስቦ እንደሚውል ተነግሯል ።

“አገልግሎቱን ለተጠቃሚዎች በእኩልነት ተደራሽ ማድረግ ” በሚል መርህ ቃል በኢትዮጵያ ሲከበር ፍትሃዊ ተደራሽነትን ማረጋገጥ ፣ ኤድስን መግታት እና ወረርሽኙን መቆጣጠርን ታሳቢ ባደረገ መልኩ እንደሚከበር የፌደራል ኤች አይ ቪ ኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ ጽ/ቤት የዘርፈ ብዙ ምላሽ ማስተባበሪያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ክፍሌ ምትኩ ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል ።

በአሁኑ ወቅት በወሲብ ንግድ ላይ የተሰማሩ ሴቶች በብዙ ተጋላጭ መሆናቸውን ሃላፊው በተጨማሪነት ተናግረዋል ።

በወሲብ ንግድ ላይ ተሰማርተዋል ተብለው ከሚታሰቡ 210 ሺህ ገደማ ሴቶች ውስጥ የተመረመሩት 113 ሺህ 619 ሲሆኑ ከእነዚህ ውስጥ 3.5ከመቶዎቹ ቫይረሱ በደማቸው እንደሚገኝ ተረጋግጧል ።

በዓለም አቀፍ ደረጃ 79 ሚሊዮን ገደማ ዜጎች ከቫይረሱ ጋር ሲኖሩ 37 ሚሊዮን ገደማዎቹ ደግሞ ህይወታቸውን ማጣታቸው ተነግሯል።

ናትናኤል ሀብታሙ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *