መደበኛ ያልሆነ

ህዳር 21፤2014-በዩጋንዳ አውሮፕላን ውስጥ የፌንጣ ምግብ ሲሸጥ የነበሩ ሰራተኞቹ ከስራ ታገዱ

በዩጋንዳ አውሮፕላን ውስጥ የፌንጣ ምግብ ሲሸጥ የነበሩ ሰራተኞቹ ከስራ ታገዱ

የዩጋንዳ ብሄራዊ አየር መንገድ በሳምንቱ መጨረሻ በአንድ በረራ በአካባቢው የሚገኝ የፌንጣ ጣፋጭ ምግቦችን ሲሸጡ የነበሩትን ሰራተኞቹን ከስራ አግዷል፡፡የዩጋንዳ አየር መንገድ እንደገለፀው በአካባቢው ኔሴኔን በመባል የሚታወቀው የፌንጣ ጣፋጭ ምግብ ሽያጭ የብሔራዊ አየር መንገዱን መንፈስ ይቃረናል ብሏል፡፡

አየር መንገዱ ይህዉ የሽያጭ ድርጊቱ አንዳንድ ተሳፋሪዎችን በበረራ ላይ ሳሉ ያልተገራ የገበያ ልምድ እንዲያደርጉ አጋልጧቸዋል ሲል አስታዉቋል፡፡ከፌንጣ ጣፋጭ ምግብ ሽያጭ ጋር በተያያዘ አንዳንድ የአየር መንገዱ ሰራተኞች ከስራ መታገዳቸውን የዩጋንዳ የሀገር ውስጥ የመገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

አየር መንገዱ በዚህ ሰሞን ፌንጣዎች በብዛት የማይገኙበት መሆኑን በመግለጽ የደንበኞች ፍላጎትን ግን ተረድተናል፤ በተጠየቀ ጊዜ የፌንጣ ምግብን ወደ ምግብ ዝርዝር(ሜኑ) ዉስጥ ለማካተት ማሰቡን አሳዉቋል፡፡እርምጃዉ የቱሪዝም ግብይትን እና በፌንጣ እሴት ሰንሰለት ውስጥ ያሉትን ህዝቦች መተዳደሪያ ያሳድጋል ሲል አየር መንገዱ አሳዉቋል።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *