መደበኛ ያልሆነ

ህዳር 21፤2014-ዓመታዊው የአዳዲ እና የአብማ ማርያም ንግስ በአል በሰላም መጠናቀቁ ተገለጸ

ዓመታዊው የአዳዲ እና የአብማ ማርያም ንግስ በአል በሰላም መጠናቀቁ ተገለጸ

በደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር በየአመቱ በድምቀት ከሚከበሩ የሀይማኖት በዓላት መካከል በጸርሐ ፅዮን አብማ ማርያም ካቴድራል ቤተክርስቲያን ህዳር 21 የሚከበረው የአብማ ማርያም ክብረ በአል አንዱ ነው፡፡

ክበረ በዓሉ በፀጥታ ሀይሉ እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ፖሊስ ባደረገው ቅድመ ዝግጅት በሰላም መጠናቀቁ ተገልጿል፡ በክብረ በዓሉ ከ150ሺ በላይ ሰዎች እንደተገኙ የተነገረ ሲሆን ከምዕመናን ስርቆት ሲፈጽሙ የነበሩ ሶስት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸው የደብረ ማርቆስ ከተማ የ1ኛ ፖሊስ ጣቢያ ወንጀል መከላከል ክፍል ሀላፊ ኢንስፔክተር ጌታቸው ባዘዘው በተለይ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡

በሌላ በኩል በኦሮሚያ ክልል ደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ቀርሳ መሊማ ወረዳ አዳዲ ከተማ ለሚከበረው አዳዲ ማርያም ክብረ በዓል ፣ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት በመደረጉ በአሉ በሰላም መጠናቀቁም የወረዳው ፖሊስ አዛዥ ዋና ኢንስፔክተር አበራ ታዬ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡ በክብረ በዓሉ ከ50 ሺ በላይ ሰዎች እንደተገኙ ኢንስፔክተር አበራ ታዬ ጨምረው ለጣቢያችን ተናግረዋል፡፡

ሳምራዊት ስዩም

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *