መደበኛ ያልሆነ

ህዳር 22፤2014-ላስታ ላሊበላ በኢትዮጵያ ጦር ቁጥጥር ውስጥ ገባች!

#ሰበር_ዜና!

የጋሸናን ግንባር ምሽጎች ሰብረው የአሸባሪውን አከርካሪ የሰበሩት የመከላከያ ሠራዊት፣ የአማራ ልዩ ኃይል፣ ሚሊሻና ፋኖ ታሪካዊቷን የላስታ ላሊበላ ከተማንና የላሊበላ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያን ተቆጣጠሩ።

በዓለም ቅርስነት የተመዘገቡ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት የሚገኙባትን የላሊበላ ከተማንና ዓለም አቀፍ የአውሮፕላን ማረፊያውን ለመቆጣጠር የተቻለው በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ መሪነት በየግንባሩ የተጀመረው ማጥቃት ውጤት ለማስመዝገብ በመቻሉ ነው።

ጀግኖቹ የመከላከያ ሠራዊት፣ የአማራ ልዩ ኃይል፣ ሚሊሻና ፋኖ የላስታ ላሊበላን አካባቢ በማጽዳት የሰቆጣ ከተማን ለመቆጣጠር ወደፊት እየገሠገሡ ነው።

ራሳቸውን በጠላት እንዳላስደፈሩት የግዳንና የራያ ወረዳዎች ሁሉ ቀሪዎቹ በወረራ ሥር የሚነገኙ የዋግ ሕምራ፣ የሰሜንና የደቡብ ወሎ ሕዝብ፣ ከጀግኖቹ የመንግሥት የጸጥታ አካላት ጋር በመሆን ጠላትን እንዲደመስስና ነጻነቱን እንዲያስከብር መንግሥት ጥሪ ያቀርባል።

የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *