መደበኛ ያልሆነ

ህዳር 22፤2014-በባህር ዳር ከተማ ከቻይናው የግንባታ ተቋም ዝርፊያ የፈጸሙ ግለሰቦች በእስራት ተቀጡ

በባህርዳር ከተማ ቀበሌ 09 አካባቢ ከሌሊቱ ዘጠኝ ሰዓት ላይ የቻይናው ሲሲሲ ከሚያስገነባው ከአባይ ማዶ ወደ ቀበሌ ዘጠኝ የሚተላለፍ የድልድይ ግንባታ ዉስጥ በድርጅቱ የሚሰሩ ዘጠኝ የግንባታ እና የጥበቃ ሰራተኞች በመመሳጠር ለግንባታ የሚያገለግል በግምት 45 ሺህ ብር የሚያወጣ ፌሮ ብረት ሰርቀዋል፡፡

ፖሊስ ወንጀሉን ሲመረምር ቆይቶ ዘጠኙን ተከሳሾች ማለትም አምስት በጥበቃ ስራ ላይ ተሰማርተው የነበሩ እና አራት ደግሞ የግንባታ ስራ ሰራተኞች በቁጥጥር ስር ዉለዋል፡፡ፖሊስ ምርመራውን ሲያጣራ ቆይቶ የባህርዳር ከተማ ወረዳ ችሎት በእያንዳንዳቸው ላይ የአምስት አመት ጽኑ እስራት መወሰኑን የባህርዳር ከተማ ፖሊስ ጣቢያ የወንጀል ምርመራ ክፍል መርማሪ የሆኑት ዋና ሳጅን ዘላለም ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡

አያይዘውም በባህር ዳር ከተማ ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ጋር በተያያዘ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል በየአካባቢው የሰፈሩን ሰላም ለማስከበር ከፖሊስ ጎን በመሆን እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

በኤደን ሽመልስ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *