መደበኛ ያልሆነ

ህዳር 23፤2014-በሀዋሳ ከተማ የተጣለዉን የሰዓት ገደብ የተላለፉ 100 አሽከርካሪዎች ተቀጡ፡፡

በሀዋሳ ከተማ የተጣለዉን የሰዓት ገደብ የተላለፉ 100 አሽከርካሪዎች ተቀጡ፡፡

በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር የሲዳማ ክልል ኮማንድ ፖስት በኩል የተጣለውን የሰአት እላፊ፣ የእንቅስቃሴዎች ገደብ የጣሱ 100 አሽከርካሪዎች መቅጣቱን የከተማዋ የፀጥታ ቢሮ አስታውቋል፡፡

የእንቅስቃሴ ገደቡን የጣሱት 280 የህዝብ ትራንስፖርትና ታክሲዎች እና የግል ተሸከርካሪዎች ሲሆኑ ቀሪዎቹ ባለሁለት እግር ተሽከርካሪ ሞተር ሳይክል እና በተለምዶ ባጃጅ የሚባሉት ባለ ሶስት እግረፍ ተሽከርካሪ መሆናቸውን የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ጸጥታ መምሪያ ኃላፊ አቶ መኩሪያ መኒሳ ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል፡፡

በተመሳሳይ በከተማዋ ከፀጥታ ከማስከበር ጋር ተያይዞ ከአሸባሪዎቹ ህውሀት እና ሸኔ ጋር ግንኙነት ይኖራቸዋል ተብለው ተጠርጥረው የተያዙ 84 ሰዎች መኖራቸውን ያነሱት ኃላፊዉ ከነዚህ ውስጥ የማጣራት ስራ በመስራት 20 የሚሆኑት በዋስትና ከእስር መለቀቃቸዉን ተናግረዋል፡፡

ከጦር መሳሪያ ጋር በተያያዘም ማንኛውም ሰው በእጁ የሚገኝ የጦር መሳሪያ እንዲያስመዘግብ ክልሉ ያስተላለፈውን መልክት በመቀበል እስካሁን 694 ሰዎች የጦር መሳሪያን አስመዝግበዋል፡፡

በትግስት ላቀዉ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *