መደበኛ ያልሆነ

ህዳር 24፤2014-በደብረ ብርሃን በሚገኙ መጠለያ ጣቢያዎች ውስጥ ጅምላ ጨራሽ ቦምብና ድምፅ አልባ መሳሪያን ይዘው የተገኙ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ ❗️

በሰሜኑ የኢትዮጲያ ክፍል ባለው ውጊያ የተነሳ ከደሴ ኮምቦልቻ ፣ ወልድያ ፣ አላማጣ፣ ሰቆጣ እና ከሌሎችም አከባቢዎች ተፈናቅለው በደብረ ብርሃን የተጠለሉ ተፈናቃዮች ቁጥር ከአንድ መቶ ሺህ ማለፉን የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባና የቴክኒክና ሙያ ልማት ኢንተርፕራይዝ ፅ/ቤት ሃላፊ አቶ አካሉ ወንድሙ ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል ።

ተፈናቃዮቹ በአስር የመጠለያ ጣቢያዎች እና በግለሰብ መኖሪያ ቤቶች ውስጥ ተጠልለው እንደሚገኙ ሃላፊው አንስተዋል ።በአሁን ሰዓት የደብረ ብርሃን ከተማ በኮማንድ ፖስት ዕዝ እየተመራች ትገኛለች ያሉት አቶ አካሉ ከ500 በላይ በጎ ፍቃደኞች በመጠለያ ጣቢያዎች ውስጥ ሊደርሱ የሚችሉ ችግሮችን እንዲለዩ ማድረጋቸውን አስታውቀዋል ።

በዚህ ሂደትም በተሰራው ስራ በተፈናቃይ መጠለያ ጣቢያዎች ውስጥ ጅምላ ጨራሽ ቦምቦችን ጨምሮ ድምፅ አልባ የጦር መሳሪያዎችን ይዘው የተገኙ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው እየተጣራ ይገኛል።ከእዚህ ባለፈ በከተማዋ ሰርገው የገቡ ከ15 የማያንሱ የኦነግ ሸኔ አባላት በቁጥጥር ስር ውለው ህጋዊ ማጣራት እየተካሄደባቸው እንደሚገኝ ምክትል ከንቲባው አቶ አካሉ ወንድሙ በተጨማሪነት ለጣቢያችን ተናግረዋል ።

በናትናኤል ሀብታሙ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *