መደበኛ ያልሆነ

ህዳር 24፤2014-በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በታክሲ ውስጥ የሚፈጸም እገታን ለመቆጣጠር የሚያግዝ መተግበሪያ(አፕሊኬሽን) ተሰራ❗️

በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ሁለት ሴት ሥራ ፈጣሪዎች የታክሲ ተጠቃሚዎችን ደህንነት ለመጠበቅ የሚረዳ የሞባይል መተግበሪያን ሰርተዋል፡፡ ኡርሱላ ንዶምቤሌ እና ማጋሊ ቡዬሳዲላ የተባሉት ስራ ፈጣሪዎቹ መንገደኞች ስለሾፌሩ መረጃ እንዲያገኙ የሚያግዝ መተግበሪያን እዉን አድርገዋል፡፡

ተጠቃሚዎቹ ስለ ጉዞአቸው ሁሉንም መረጃ ለማግኘት በታክሲው ላይ ያለውን ኪዉአር ኮድ በስልኮቻቸዉ ስካን ያደርጋሉ፡፡እስካሁን አንድ ሶስተኛው የኪንሻሳ ታክሲ አሽከርካሪዎች በመመዝገባቸዉ የደህንነት ሁኔታዉን አስተማማኝ ያደርገዋል፡፡

የታክሲ አሽከርካሪዎች ደንበኞቻቸው እንዲያምኗቸዉ የበለጠ ስለሚረዳቸዉ ለንግድ ስራቸዉ መልካም ሆኖ ማግኘታቸዉን ይናገራሉ፡፡በኪንሻሳ በታክሲ ዉስጥ እገታና አፈና የተለመደ ነው።

ፖሊስ በየሳምንቱ እስከ አምስት የሚደርሱ እገታ መፈጸሙን ሪፖርት እንደሚደረግለት መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ ነገር ግን ባለፈው ወር ወደ አምስት ዝቅ ማለቱ ተነግሯልለ፡፡መተግበሪያዉ ሆጃ የሚሰኝ ሲሆን ስራ ፈጣሪዎቹ ወደ ሌሎች የአፍሪካ ከተሞች ስራቸዉን ለማስፋት ማለማቸዉን ይናገራሉ፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *