መደበኛ ያልሆነ

ህዳር 24፤2014-ብስራት ሬዲዮ በጦር ሀይሎች ኮምፕሪሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ለሚገኙ የጦር ጉዳተኞች ድጋፍ አደረገ❗️

የመከላከያ ሰራዊት ኢትዮጵያ አሁን ካለችበት ሃገራዊ ሁኔታ ጋር በተያይዘ የሰላም ማስከበር ግዴታ ላይ እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡ሆኖም ለህይወታቸው ሳይሳሱ የኢትዮጲያን እንዲሁም የህዝቦቿን ሰላም ለማስከበር የራሳቸውን ህይወት አደጋ ላይ በመጣል እንቅስቃሴ በሚያደርጉበት ወቅት አደጋ ለደርሶባቸው በሆስፒታል ለሚገኙ ታካሚዎች የብስራት ሬዲዮ ጋዜጠኞና የአስተዳደር ሰራተኞች በስፍራዉ በመገኘት መከላከያ ሰራዊቱን ለመደገፍ እንዲሁም ከጎናችሁ ነን ለማለት የሴቶች የንጽህና መጠበቂያ እና የፍራፍሬ ጭማቂ አበርክቷል

በጦርሃይሎች ኮምፕሪሄንሲቭ ሆስፒታል የስነ አዕምሮ ባለሙያ እንዲሁም የማህበራዊ ኮሚቴ አባል የሆኑት ሻለቃ አስካለ የህብረተሰቡ ድጋፍ ለመከላከያ ሰራዊቱ ትልቅ አለኝታ እነደሆነ በመግለጽ አይዞችሁ ከማለት ባለፈ በአይነ፣ በገንዘብ እና በሞራል ጭምር ትልቅ ድጋፍ እያደረገ መሆኑን ከብስራት ራዲዮ ጋር በነበራቸው ቆይታ ተናግረዋል፡፡

አያይዘውም ይህ ጊዜ ሁሉም ሰው ኢትዮጵያን በመተባበር ለመገንባት አንድ መሆን ያለበት ከመሆኑም ባሻገር አይበገሬውን የመከላከያ ሰራዊት በመተባበር የምንደግፍበት ጊዜ መሆን አለበት ሲሉ ሻለቃ አስካለ ጨምረዉ ለብስራት ራዲዮ ተናግረዋል፡፡

በኤደን ሽመልስ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *