መደበኛ ያልሆነ

ህዳር 24፤2014-የሊቢያ ፍርድ ቤት የጋዳፊ ልጅ የፕሬዝዳንትነት እጩ ሆነዉ እንዲወዳደሩ ወሰነ ❗️

የሊቢያ የረዥም ዓመታት ገዥ ሙአመር ጋዳፊ ልጅ በሀገሪቱ በሚካሄደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ እንዲወዳደር ፍቃድ ተሰጥቶታል ሲሉ የሰይፍ አል ሲስላም ጋዳፊ ጠበቃ ተናግረዋል፡፡የሊቢያ ባለስልጣናት በአባቱ ላይ በተነሳው ህዝባዊ አመጽ የጦር ወንጀል ፈጽሟል በሚል ሰይፍ አል ኢስላም ጋዳፊ ከሳምንት በኋላ ከምርጫዉ እንዲገለል ማድረጋቸዉ ይታወሳል፡፡

የሰይፍ አል እስላም ጋዳፊ ጠበቃ ኻሊድ አል-ዛይዲ እንዳረጋገጡት በሴባ ከተና የሚገኘው ፍርድ ቤት የደንበኛቸዉን ይግባኝ ተቀብሎ ሊካሔድ በታቀደው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ወደነበሩበት እንደሚመለሱ ማረጋገጫ መስጠቱን ተናግረዋል፡፡ የጋዳፊ ልጅ ባለፈዉ ሳምንት በሴብሃ ይግባኝ ሲያቀርቡ አንድ ህገ-ወጥ ቡድን ወደ ፍርድ ቤት ዘልቆ በመግባት ጥቃት የሰነዘረ ሲሆን ይግባኙን ለመስማት ሰአታት እንዲዘገይ አስገድዶ ነበር፡፡

ሰይፍ አል ኢስላም በምርጫው ከተመዘገቡ እጩዎች መካከል ለአሸናፊነት በከባድ ሚዛን ከሚቀመጡት ተርታ ይገኛል፡፡ከጋዳፊ ከስልጣን መወገድ በኃላ የሊቢያ አንድነት መመለስ እንደሚፈልግ ከኒዉዮርክ ታይምስ ጋር በወርሃ ሀምሌ ባደረገዉ ቃለ መጠይቅ መናገሩ ይታወሳል፡፡

የሴብሃ ፍርድ ቤት የሰይፍ አል እስላም የምርጫ እጩነትን ውድቅ ያደረገዉን የምርጫ ኮሚሽኑን ውሳኔ በመሻር ለታህሳስ ምርጫ እንዲወዳደር ወስኗል፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *