መደበኛ ያልሆነ

ህዳር 24፤2014-የካሜሩን የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ በነበሩበት ሆቴል በቁጥጥር ስር ዋሉ

የካሜሩኑ ተቃዋሚ ፓርቲ መሪ ሞሪስ ካምቶ ባሳለፍነዉ እሮብ በሀገሪቱ ትልቋ ከተማ ዱዋላ ውስጥ በአንድ ሆቴል ውስጥ መጽሃፋቸውን ለማስመረቅ በነበሩበት ሁኔታ በቁጥጥር ስር ዉለዋል፡፡የካሜሩን ህዳሴ ንቅናቄ መሪ ቫሌ ዴ ፕሪንስ በተሰኘዉ ሆቴል በመጽሃፍ ምረቃ ስነ ስርዓት ላይ ፊርማቸዉን ለሚጠብቁ ደጋፊዎቻቸዉ ማከናወን ሳይችሉ ቀርተዋል፡፡

የሞሪስ ካምቶ እስር በደጋፊዎቻቸዉ ዘንድ ስጋት ፈጥሯል፡፡ልዩ አማካሪያቸዉ አልበርት ዲዞንጋንግ በበኩላቸዉ ለሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን እንደተናገሩት በስልክ አዉርተናል በመልካም ሁኔታ ላይ ይገኛሉ ሲሉ ተደምጠዋል፡፡

የካምቶ እንቅስቃሴ አማካሪ እንደሚሉት ካምቶ ሚስጥራዊ ትዕዛዝ ሰጪ በሆነ ሀይል መመሪያ መሰረት በፖሊስ በቁጥጥር ስር መዋላቸዉን ገልጸዋል፡፡የተቃዋሚው ፓርቲ መሪ ከዚህ ቀደም በባለሥልጣናት ትዕዛዝ በቁጥጥር ስር መዋላቸዉ ይታወሳል፡፡

የመንግስት ተቺ በሆኑ ተቃዋሚዎች ላይ ኢ-ፍትሃዊ በሆነ መልኩ ከዚህ ቀደም እንዲጠየቁ መደረጉ አይዘነጋም፡፡በአንግሎ ሮን እን ፍራክኖ ፎን ግዛቶች የሚታወሳዉን የካሜሮን ፓለቲካን አለመረጋጋትና ዉጥረት ቢያነግስም ከሶስት አስርት ዓመታት በላይ አዛዉንቱ ፕሬዝዳንት ፓል ቢያ ሀገሪቱን በመምራት ላይ ይገኛሉ፡፡

በሚኪያስ ጸጋዬ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *