መደበኛ ያልሆነ

ህዳር 24፤2014-የፍልስጤም አስተዳደር ለመንግስት ሰራተኞች ደሞዝ ለመክፈል እጅ እያጠረዉ መሆኑ ተሰማ

ከዓመታት የኢኮኖሚ መቀዛቀዝ በኋላ፣ የዌስት ባንክ አስተዳደር ለመንግስት ሰራተኞች ደሞዝ ለመክፈል ከፍተኛ ዳገት እንደሆነበት ተነግሯል፡፡የዋጋ ግሽበት፣ የለጋሾች እርዳታ መቀነስ እና እስራኤል የታክስ ገቢን መከልከሏ ለፍልስጤም አስተዳደር ቀድሞውንም የነበረዉን የበጀት ጉድለት ይበልጡኑ አባብሶታል፡፡

የምንገኝበት ሁኔታ አስቸጋሪ ነዉ፣ የፋይናንስ እጥረት አለብን ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር መሀመድ ሽታይህ በዚሁ ሳምንትለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል፡፡ ደሞዝ ለመክፈል እርዳታ አላገኘንም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስተሩ ወርሃዊ የደሞዝ ወጪ 292 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር እንደሚገመት ተናግረዋል፡፡

እ.ኤ.አ በ1993 የፍልስጥኤም አስተዳደር ከተመሠረተበት ጊዜ ጀምሮ በባለስልጣኖናት እና ተንታኞች የተገለፀው ዓይነት የፋይናንስ ቀውሱ ሲመዘገብ ለመጀመሪያ ጊዜ ነዉ፡፡መጀመሪያ ላይ ምንም ክፍያ እንደማንቀበል ተነግሮን ነበር፡፡ከዚያም ከደመወዛችን ላይ በቋሚነት 25 በመቶ ቅናሽ ልናገኝ እንደምንችል ተነገረን። ከዚያ በኋላ፣ 25 በመቶው የሚቀነሰው ለጥቂት ወራት ብቻ ነው ተብለን ነር ሲሉ አንድ የፍልስጥኤም አስተዳደር ሠራተኛ ለአልጀዚራ ያለዉን ችግር ተናግሯል።

በሚኪያስ ጸጋዬ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *