መደበኛ ያልሆነ

ህዳር 27፤2014-በጋምቢያ በተደረገው ምርጫ ፕሬዝዳንት አዳማ ባሮው እየመሩ መሆኑ ተሰማ

የጋምቢያ የምርጫ ኮሚሽን ይፋ ባደረገው ከፊል የመራጮች ውጤት ተከትሎ የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት አዳማ ባሮው ለድሉ መቃረባቸውን አስታውቋል። በምርጫ ኮሚሽኑ የቀረበውን ውጤት ሶስት እጩዎች ውድቅ በማድረግ እንደማይቀበሉት ገልፀዋል።

ባሮው 54 በመቶ የመራጮች ድምፅ ማግኘት የቻሉ ሲሆን የ2.5 ሚሊዮን ህዝቦች የመኖሪያ ሀገር የሆነችውን ጋምቢያን በድጋሚ የመምራት እድል ያገኛሉ።በምርጫው ከስድስቱ እጩዎች ውስጥ ለአሸናፊነት አብላጫ ድምፅ ማግኘት አሸናፊ ያደርጋል።

በጋምቢያ ከ27 ዓመታት በኃላ ለመጀመሪያ ጊዜ ሀገሪቱን ለ22 ዓመታት የመሩት በስደት ኢኳቶሪያ ጊኒ የሚገኙት ያህያ ጃሜ ያልተሳተፉበት ምርጫ ሆኖ ተመዝግቧል።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *