መደበኛ ያልሆነ

ህዳር 28፤2014-ለአፋር ሕዝባዊ ሰራዊት በገዋኒ የጀግና አቀባበል ተደረገላቸው

ከአገር መከላከያ ሰራዊት ጋር በመሆን በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት በአሸባሪት የተፈረጀውን የሕወሓት ቡድን ከአፋር ምድር በማፅዳት ከፍተኛ ጀብድ የፈፀሙት የአፋር ሕዝባዊ ሰራዊት በገዋኒ ወረዳ የጀግና አቀባበል ተደረገላቸው፡፡

በአፋር ክልል የህወሃት ቡድንን አይቀጡ ቅጣት በመቅጣት ተአምራዊ ጥቃት ከፈፀሙት የፀጥታ ኃይሎች መካከል የአፋር ሕዝባዊ ሰራዊት አንደኛው መሆኑ ይታወቃል።

ይህ ሰራዊት ህወሃት በሁሉም ጦርነት በከፈተባቸው ግምባሮች ከፀጥታ ኃይሎች ጋር በመቀናጀት ታላቅ ጀብዱ ሰርቷል።

ከአፋር ክልል ከሁሉም ጫፍ፣ ከሁሉም ወረዳዎች የዘመተው ሕዝባዊ ሰራዊት የአያት ቅድመ አያቱን የጀግንነት ታሪክ በመድገም በሁሉም ግምባሮች ታሪክ ሰርቷል ሲል የክልሉ ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ አስታውቀዋል።

ሕዝባዊ ሰራዊቱን ወደግምባር ከላኩት መካከል በሆነችው ገዋኒም ታጋዮች በድል ሲመለሱ የጀግና አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *