መደበኛ ያልሆነ

ህዳር 28፤2014-በሮሂንጋይ ሙስሊሞች ላይ የጥላቻ ንግግር ማስቆም አልቻለም የተባለዉ ፌስቡክ የ150 ቢሊዮን ዶላር ክስ ቀረበበት

በዩናይትድ ኪንግደም እና አሜሪካ የሚገኙ የሮሂንጊያ ስደተኞች ፌስቡክ የጥላቻ ንግግር እንዲሰራጭ ፈቅዷል በማለት ግዙፉን የማህበራዊ ሚዲያ ግዙፉ ድርጅት ከሰዋል።ፌስቡክ በተሰደዱ አናሳዎች ላይ ጥቃት እንዲፈጸም ያበረታታል በማለት ከ150 ቢሊዮን ዶላር በላይ ካሳን ጠይቀዋል።

እ.ኤ.አ. በ2017 የቡዲስት አብላጫ ባለባት ምያንማር በተደረገ ወታደራዊ ዘመቻ 10,000 የሚገመቱ የሮሂንጊያ ሙስሊሞች ተገድለዋል።አሁን ላይ ሜታ እየተባለ የሚጠራው ፌስቡክ ለቀረበበት ክስ ምላሽ ከመስጠት ተቆጥቧል።

በክሱ ላይ ኩባንያዉ ጥላቻ እና አደገኛ የሆኑ የተሳሳቱ መረጃዎች እንዲሰራጩ ለዓመታት እንዲቀጥል ፈቅዷል የሚል ቀርቧል፡፡ኩባንያው በሮሂንጊያ ላይ ጥቃት የሚቀሰቅሱትን ልጥፎችን ማውረድ ወይም መሰረዝ አልቻለም በበጎ አድራጎት ድርጅቶች እና በመገናኛ ብዙሃን ማስጠንቀቂያ ቢሰጥም ተገቢ እና ወቅታዊ እርምጃ መውሰድ አልቻለም መባሉ ቁጣን ቀስቅሷል፡፡

ፌስቡክ በምያንማር ከ20 ሚሊዮን በላይ ተጠቃሚዎች ያሉት ሲሆን ለአብዛኛዉ ህዝብ የማህበራዊ ድህረ-ገጹ ዋንኛ የዜና ምንጭ ማጋሪያ ነዉ፡፡ከዚህ ቀደም ፌስቡክ በ2018 በሮሂንጊያዎች ላይ የሚደርሰውን ጥቃት እና የጥላቻ ንግግር ለመከላከል በቂ ስራ እንዳልሰራ መናገሩ ይታወሳል፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *