መደበኛ ያልሆነ

ህዳር 28፤2014-በቦረና በተከሰተው ድርቅ ብርቅዬ የዱር እንስሳት ለአደጋ መጋለጣቸው ተገለጸ

በቦረና ዞን በተከሰተው ድርቅ ምክንያት፣ በዞኑ በሚገኘው ቦረና ብሔራዊ ፓርክ የሚገኙ ብርቅዬ የዱር እንስሳት ለአደጋ መጋለጣቸው ተገልጸ። በድርቁ ምክንያት በአካባቢው ከፍተኛ የግጦሽና የውኃ እጥረት በመኖሩ እንስሳቱ ለአደጋ መጋለጣቸው ተሰምቷል።

የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልል፣ የዱር እንስሳት ፓርኮች እና ኢኮቱሪዝም ዳይሬክተር መሐመድ ኑር ጀማል ለአዲስ ማለዳ እንደገለጹት፣ በምስራቅ አፍሪካ ኢትዮጵያና ኬንያ ብቻ ከሚገኙ የሜዳ አህያ ዝርያዎች አብዛኞቹ በቦረና ብሔራዊ ፓርክ እንደሚገኙ ጠቁመው፣ አሁን ላይ በዞኑ ባለው ድርቅ ምክንያት የዱር እንስሳቱ የውኃ እጥረት እንዳጋጠማቸው አመላክተዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *