መደበኛ ያልሆነ

ህዳር 30፣2014-ህወሓት በትራንስፖርት መሰረተ ልማቶች ላይ ያደረሰዉን ጉዳት መልሶ ለመጠገን ስራዎች እንደሚሰሩ የትራንስፖርት ሚኒስቴር አስታወቀ

አሸባሪዉ ህወሓት በትራንስፖርት መሰረተ ልማቶች ላይ ባደረሰዉ ጉዳት የተለያዪ አገልግሎቶች እንዲስተጓጎል ምክንያት ሆኗል፤ ያደረሳቸዉን ዉድመቶች መልሶ አገልግሎት እንዲሰጥ የማድረግ ስራን በቀጣይ ለመስራት ዝግጅቶች እየተደረገ እንደሚገኝ የትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ ሚኒስቴር የኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር እንዳልካቸው ፀጋዬ ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል።

የሽብር ቡድኑ በላሊበላ አየር ማረፊያ እና በተለያዩ የትራንስፖርት መሰረተ ልማቶች ላይ ያደረሰዉን ዉድመት መልሶ ለመጠገን ከመንግስት በተጨማሪ በልማት አጋር አካላት እና በግሉ ባለሀብት መታገዝ እንደሚገባ የኮሚኒኬሽን ዳይሬክተሩ አንስተዋል ።

በተጨማሪም የትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ ሚኒስቴር በአፋር ክልል ለሚገኙ ተፈናቃዮች የ10 ሚሊዮን 400 ሺህ ብር ድጋፍ ማድረጉን አቶ እንዳልካቸው ፀጋዬ ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል።

በክልሉ ለሚገኙ ተፈናቃዮች የዱቄት፣ ዘይት ፣ አንሶላ ፣ ፍራሽ እና ሌሎች አስፈላጊ ግብአቶችን ድጋፍ መድረጉንም አስታዉቀዋል ። ከ90 በመቶ በላይ የኢትዮጵያ የዉጪ ንግድ የሚተላለፈዉ በክልሉ ሲሆን መከላከያ ሰራዊቱ እና የክልሉ የጸጥታ አካላት በጋራ ባደረጉት ተጋድሎ የአሸባሪዉ አላማ እንዳልተሳካ ገልፀዋል።

በበረከት ሞገስ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *