መደበኛ ያልሆነ

ህዳር 30፣2014-የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ለጉብኝት በሄዱበት ካንሳስ ከተማ ከኢትዮጵያውያን ከፍተኛ ተቃውሞ ገጠማቸው ❗️

በካንሳስ ከተማ ነዋሪ የሆኑ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን “የጆ ባይድን አስተዳደር በሀገር ውስጥ ጉዳያችን ጣልቃ መግባታቸውንና አሸባሪው ህወሃትን የመደገፍ እንቅስቃሴውን ሊያቆም ይገባል ፣ ይበቃል #NoMore” ብለዋል።

ፀደንያ ተስፋዬ እና ሄኖክ ተከስተ የተባሉ የተቃውሞ ሰልፏ ፊት አውራሪዎች “በዲሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጠ መሪ አለን ፣ ጦርነቱም ያበቃለት ጉዳይ ነው ጣልቃ ገብነቱ ያበቃል” ሲሉ ለKMBC 9 News ድምፃቸውን አሰምተዋል።

የባይደን አስተዳደር ከኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ብቻም ሳይሆን ከሀገሬው ዜጎችም በደቡባዊው የሀገሪቱ ክፍል በሚገኘው ድንበር ፣ በአፍጋኒስታን ጉዳዩና ኮቪድ-19 መከላከል ዙሪያ ተቃውሞ ገጥሟቸዋል።

ሚኪያስ ፀጋዬ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *