መደበኛ ያልሆነ

ህዳር 30፣2014-የገቢዎች ቢሮ የግብር ከፋዮችን የቤት ለቤት ጉብኝት ፕሮግራም ይፋ አደረገ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ ባለፉት አራት ወራት ሊያሰባስበው ካቀደው 20 ቢሊዮን ብር 25 ቢሊዮን ብር በማሰባሰብ የዕቅዱን 118 % ያሳካ ሲሆን ይህ በግብር ሰብሳቢውና በንግዱ ማኅበረሰብ መካከል እያደገ ያለውን በጎ ግንኙነት ይበልጥ ለማሻሻል ያለመ የግብር ከፋዮች የቤት ለቤት ጉብኝት ማስጀመሪያ ፕሮግራም ይፋ ሆኗል፡፡

በተጠቀሱት ወራት የግብር አሰባሰብ ሂደት ላይ የላቀ አፈፃፀም ካስመዘገቡት ቅርንጫፎች መካከል የመጀመሪያው በሆነው በአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ አራዳ አነስተኛና መካከለኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ይፋ በተደረገው ፕሮግራም ላይ የቢሮው ኃላፊ ክቡር አቶ ሙሉጌታ ተፈራ “በግብር ሰብሳቢው መስሪያ ቤትና በግብር ከፋዩ ማኅበረሰብ ዘንድ ቀደም ሲል የነበረው ግንኙነት ባለመተማመን ላይ የተመሰረተ እንደነበር ገልፀው ይህ አካሄድ አንድ ጠንካራ ሀገር የመገንባት ትልም ላለው ሁለት ግን አንድ አካል አጥፊ አተያይ መሆኑን በቅጡ በመረዳት ይህንን እሳቤ የመቀየር ስራ እየሰራን ነው” ብለዋል፡፡

ቢሮው የግብር ከፋዮች የቤት ለቤት ጉብኝት ፕሮግራም ባስጀመረበት ወቅት በተመረጡ የደረጃ ‹‹ሀ፣ ለ እና ሐ›› ግብር ከፋዮች ዘንድ የቤት ለቤት የስራ ቦታ ጉብኝት ተደርጓል።
ጉብኝት የተደረገባቸው ግብር ከፋዮች ግብር ሰብሳቢው መስሪያ ቤት ግብር ከፋዩን ማኅበረሰብ በጥርጣሬ ከማየት አልፎ በዚህ ደረጃ መቀራረብ መፈጠሩ የሚበረታታ ነዉ ብለዋል ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *