መደበኛ ያልሆነ

ታህሳስ 1፤2014-የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች ላይ የታሪፍ መጠን እንደሚሻሻል የትራንስፖርት ቢሮ አስታወቀ

የዓለም አቀፍ ነዳጅ ምርቶች መሸጫ ዋጋ እየጨመረ ከመምጣቱ ጋር ተያይዞ በታህሳስ ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ አዲስ የዋጋ ማስተካከያ መደረጉ ይታወሳል።
ይህንን ተከትሎ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት ቢሮ በህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ላይ የታሪፍ ማሻሻያ ለማድረግ ጥናቱን በማጠናቀቅ ላይ ሲሆን፥ በቀጣይ ቀናት ይፋ ለማድረግ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል ሲሉ የቢሮው ኮሚኒኬሽን ዳይሬከተር አቶ አረጋዊ ማሩ ለብሰራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡

በመሆኑም የታሪፍ ማሻሻያው ተጠናቆ ይፋ እስኪሆን ቀደም ሲል በነበረው የታሪፍ ዋጋ አገልግሎቱ የሚሰጥ ይሆናል ሲሉ ተናግረዋል፡፡
በከተማዋ በህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኙ አሽከርካሪዎችም የታሪፍ መጠኑ ይፋ ሳይሆን ምንም ዓይነት ዋጋ ባለመጨመር አገልግሎቱን በመስጠት ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ቢሮው አሳስቧል፡፡

በቤቴልሄም እሸቱ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *