መደበኛ ያልሆነ

ታህሳስ 1፤2014-የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አጄንሲ የደሴ ቅርንጫፍ በሽብርተኛው የህወሀት ቡድን መዘረፉ ተነገረ❗️

ከመድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ቅርንጫፎች መካከል አንዱ የሆነው የደሴ ቅርንጫፍ በሽብርተኛው የህወሀት ቡድን ከፍተኛ ዝርፊያ እና ጉዳት እንደደረሰበት ማረጋገጡን ኤጀንሲው አስታውቋል፡፡

በየሄደበት ዝርፊያ፣ ግድያ፣ ማፈናቀል እና ኢሰብዓዊ ተግባር ልዩ ባህሪው የሆነው ፀረ ህዝብ ቡድኑ በቅርንጫፉ በክምችት የነበሩ መድኃኒት እና ሌሎች የህክምና ግብዓቶችን የቻለውን በመዝረፍ ሊዘረፉ በማይችለው የመስረተ ልማት አውታሮች ላይ ከፍተኛ ውድመት ማድረሱን የኤጀንሲው የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ አወል ሀሰን ለብስራት ሬድዮ የላኩት መረጃ ያሳያል፡፡

ቅርንጫፉ በከፍተኛ መሰረተ ልማት የተደራጀ እና በአከባቢው ለ27 ሆስፒታሎች፣ ለ303 ጤና ጣቢያዎች፣ ለ60 ወረዳዎች እንዲሁም ከህግ ማስከበር ዘመቻው እስከ የህልውና ዘመቻው ድረስ በከፍተኛ ደረጃ የመድኃኒት እና ሌሎች የህክምና ግብዓት በማቅረብ አገልግሎት እየሰጠ የነበረ ነው ተብሏል፡፡

በክምችት ከነበረ ከፍተኛ ጠቀሜታ ያላቸውን መድኃኒቶች ፣ የህክምና ቁሳቁስ እና ሁሉንም ተሸከርካሪዎች ከጥፋት ቡድኑ ለማዳን ቢቻልም የተቀሩት መድኃኒት እና የህክምና ግብዓት ላይ እኩይ አላማውን ፈፅሟል፡፡

ውድመቱ በከፍተኛ መዋለ ንዋይ የተገነባ ግዙፍ የእናቶች እና ህፃናት ክትባት ግብዓት ማከማቻ የማቀዝቀዣ ሰንሰለት መጋዘን(Cold Room)፣ ዋና መጋዘን፣ ቢሮዎች፣ የማከማቻ መሰረተ ልማት፣ ፎርክሊፍቶች ፣ የደህንነት መቆጣጠሪያ ስርዓቶችን ፣ የቢሮ መሳሪያዎች እና ሌሎች ንብረቶችን ያካትታል፡፡

በአጠቃላይ በቅርንጫፉ ላይ የተፈፀመውን ውድመት በጥልቀት በማጥናት በአይነትና በገንዘብ የደረሰውን የጉዳት መጠን በቀጣይ በአገልግሎቱ ይፋ ይደረጋል።

በትዕግስት ላቀው

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *