መደበኛ ያልሆነ

ታህሳስ 2፤2014-ባቲ፣ አቀስታ፣ መሀል ሳይንት እና ሳይንት አጅባር ከተሞች የኤሌክትሪክ አገልግሎት አገኙ ❗️

አሸባሪው ሕወሃት ቡድን ባደረሰው የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ጉዳት አገልግሎት ተቋርጦበቸው የነበሩ ባቲ፣ አቀስታ፣ መሀል ሳይንት እና ሳይንት አጅባር ከተሞች በዛሬው ዕለት ኤሌክትሪክ ማግኘታቸውን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታወቀ፡፡

አሸባሪው ቡድን ባደረሰው የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ጉዳት ምክንያት የተጎዱ የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ መስመሮች የመጠገንና መልሶ የማገናኘት ስራው ተጠናክሮ እየተሰራ ሲሆን፣ የክልሉ ሰራተኞችና ማኔጅመንት አባላት እያደረጉት ባለው ከፍተኛ ትብብር ኤሌክትሪክ ተቋርጦባቸው የነበሩ ከተሞችን ኤሌክትሪክ መልሶ እንዲያገኙ መደረግ ተችሏል፡፡

በዛሬው ዕለት ጠዋት ማጀቴ ከተማ ኃይል ያገኘች መሆኗን የገለፀው አግልግሎቱ፣ ከሰዓት በኋላ ደግሞ ባቲ፣አቀስታ፣መሀል ሳይንት እና ሳይንት አጅባር ከተሞች የኤሌክትሪክ አገለግሎት እንዲያገኙ መቻሉን የአገልግሎቱ የደሴ ዲስትሪክት ዳይሬክተር አቶ ሀብቱ አበበ አሳውቀውናል ብሏል፡፡

በደሴ ዲስትሪክት ስር አገልግሎት የሚያገኙት ከሚሴ፣ኮምቦልቻ፣ደሴ እና ጨፋ ሮቢት ከተሞች የኤሌክትሪክ አገልግሎት ማግኘታቸውን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታውቋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *