
በህዳር ወር የተመዘገበው ምግብ ነክ ያልሆኑ ምርቶች የዋጋ ግሽበት ፣ ከጥቅምት ወር ጋር ሲነፃፀር አንድ በመቶ ጭማሪ ማሳየቱን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ሰላማዊት ካሳ በዛሬው እለት በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል፡፡
እንደ ሚኒስቴር ዲኤታዋ ማብራሪያ በህዳር ወር ምግብ ነክ ያልሆኑ ምርቶች የዋጋ ግሽበቱ 38.9 በመቶ የተመዘገበ ሲሆን ፣ ይህም ከጥቅምት ወር ጋር ሲነጻጸር በ1.7 በመቶ ቅናሽ ማሳየቱን አሳይቷል፡፡
በተመሳሳይም በ2014 በጀት ዓመት በህዳር ወር አጠቃላይ የዋጋ ግሽበቱ 33 በመቶ ሆኖ መመዝገቡን ሚኒስቴር ዲኤታዋ የተናገሩ ሲሆን ፣ ይህም ካለፉት ሁለት ወራት ጋር ሲነጻጸር ቅናሽ አሳይቷል ብለዋል ፡፡
ጠንካራ የማክሮ ኢኮኖሚው ለመገንባት በተወሰደው እርምጃ ፤ የገንዘብ ፖሊሲዎች እና አስተዳደራዊ ለውጦች መደረጉ በተወሰነ መልኩ የዋጋ ግሽበቱ እንዲቀንስ አስችሎታል የተባለ ሲሆን ፣ ምግብ ነክ ያልሆኑ ምርቶች ላይ የታየውን ጭማሪ ለመቀነስ በሌሎች መንገዶች የተወሰዱ እርምጃዎች በመውሰድ ተግባራዊ በማድረግ ቅናሽ እንዲያሳዩ ይደረጋል ተብሏል፡፡
ትዕግስት ላቀው