መደበኛ ያልሆነ

ታህሳስ 4፤2014-ተንታ ፣ ማሻና ወግዲ ከተሞች የኤሌክትሪክ ሃይል አገኙ

ተንታ፣ ማሻና ወግዲ የሚባሉ ከተሞች ተቋርጦባቸው የነበረው የኤሌክትሪክ አገልግሎት በድጋሚ ማግኘታቸውን የአማራ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት አሳውቋል፡፡

የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት የወደመባቸውን ከተሞች የኤሌክትሪክ አስተላላፊ መስመሮችንና ምሰሶዎችን በመጠገን ነፃ የወጡ ከተሞችን ከስር ከስር እተከተለ የኤሌክትሪክ ኃይል መልሶ የማገናኘት ስራ ተጠናክሮ መቀጠሉን ገልጿል፡፡

በዚህም ተንታ፣ ማሻና ወግዲ ከተሞች የሚያገኙበትን የመካከለኛና የዝቅተኛ መስመር ጥገና በማጠናቀቅ አገልግሎቱን ትላንትና ዛሬ ጠዋት እንዲያገኙ መደረጉን ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *