መደበኛ ያልሆነ

ታህሳስ 4፤2014-የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ናፍታሊ ቤኔት በተባበሩት አረብ ኢምሬትስ የመጀመሪያ ይፋዊ የስራ ጉብኝት ጀመሩ

የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ናፍታሊ ቤኔት የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ የሚገኙ ሲሆን ከእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ኢሚሬቶችን የጎበኙ የመጀመሪያው መሪ እንደሚያደርጋቸው መሆኑን ቃል አቀባያቸው ተናግረዋል።ቤኔት በዛሬው እለት ከአልጋ ወራሹ ልዑል ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን ጋር ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል።

መሪዎቹ በእስራኤል እና በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ መካከል ያለውን ግንኙነት በተለይም ኢኮኖሚያዊ እና ክልላዊ ጉዳዮችን በጥልቀት ስለማስቀጠል ይወያያሉ።ሁለቱ ሀገራት የክፍለ ዘመኑ ስምምነት በተባለው የአብርሃም ስምምነት ይፋዊ ግንኙነት መጀመራቸው ይታወሳል።

የሀገራቱ ግንኙነት በአለም ሀያል ሀገራት እና በኢራን መካከል የሚደረገውን የኒውክሌር ድርድር በመቃወም የተደረገ የሚሉ መረጃዎች እየወጡ ይገኛል።

በሚኪያስ ፀጋዬ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *