መደበኛ ያልሆነ

ታህሳስ 5፤2014-ኦሮሚያ ባንክ የይቀበሉ ይመንዝሩ ይሸልሙ መርሃ ግብሩን አጠናቅቆ የእጣ ማውጣት መርሃ ግብር አካሄደ

ኦሮሚያ ባንክ የውጪ ምንዛሬን ለማሳደግ ለሶስተኛ ጊዜ አዘጋጅቶት የነበረውን እንዲሁም ለስምንት ወራት የቆየውን የይቀበሉ፣ ይመንዝሩ እና ይሸልሙ መርሃ ግብሩን ያጠናቀቀ ሲሆን የእጣ ማውጣት ስነ ስርዓት በብሔራዊ ሎተሪ አካሂዷል ።

ኦሮሚያ ባንክ ባዘጋጀውየይቀበሉ ይመንዝሩ ይሸልሙ መርሃ ግብር ላይ ዲያስፖራው ትክክለኛውን እና ተገቢውን አገልግሎት በመጠቀም የቁጠባ ባህሉን ማሳደግ እንዲሁም ደግሞ በኢትዮጲያ እየተስፋፋ ያለውን የህገወጥ የገንዘብ ዝውውር ለመግታት ትክክለኛው አማራጭ እንደሆነ ተመልክቷል። በእጣ አወጣጥ መርሃ ግብሩ ላይ እጣው ለደረሳችው የባንኩ ደንበኞች የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክታቸወን የኦሮሚያ ባንክ ፕሬዝዳንት አቶ ተፈሪ መኮነን ገልጸዋል።

የእጣው አይነት አንደኛ እጣ አይሱዙ ተሽከርካሪ ሁለተኛ እጣ አራት ባለ ሶስት እግር ተሽከርካሪ ሶስተኛ እጣ አራት የሞተር ሳይክል ሲሆን አራተኛ እጣ የውሃ መሳቢያ ሞተር እና አምስተኛ እጣ 16 ሶላር ጨምሮ 40 የሞባይል ቀፎዎች ናቸው።

የኦሮሚያ ባንክ የይቀበሉ ይመንዝሩ ይሸልሙ አራተኛ ዙር መርሃ ግብሩን በጥቂት ሳምንታት ውስጥ እንድሚጀምር የኦሮሚያ ባንክ ፕሬዝዳንት አቶ ተፈሪ መኮነን ለብስራት ራዲዮ ተናግረዋል።

በኤደን ሽመልስ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *