መደበኛ ያልሆነ

ታህሳስ 6፤2014-በህውሃት ላይ የተወሰደው እርምጃ አዲስ አበባ የፀጥታ ችግር እንዳለ አስመስለው ሃሰተኛ መረጃ ሲያሰራጩ የነበሩ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ አድርጓል ሲል መንግስት አስታወቀ

ከሳምንታት በፊት አዲስ አበባ የፀጥታ ስጋት ያለባት አስመስለው ሃሰተኛ መረጃ ሲያሰራጩ የነበሩ አካላት ከመሰሉ ተግባሮቻቸው ተቆጥበዋል ሲል የመንግስት ኮሚዩኒኬሽ አገልግሎት አስታውቋል ፡፡

የመንግስት ኮሚዩኒኬሽ አገልግሎት በዛሬው እለት በሰጠው መግለጫ እንዳስታወቀው ከሆነ ሽብርተኛው የህውሃት ቡድን ወደ አዲስ አበባ የቀረበ የመሰላቸው የሽብር ቡድኑ ደጋፊዎች እና የውጪ ክንፎች በቡድኑ ተስፋ በመቁረጣቸው ይህንን ሃሰተኛ መረጃ ከማሰራጨት ተቆጥበዋል ሲሉ ሚኒስትር ድኤታው ከበደ ዴሲሳ ተናግረዋል ፡፡

የአሜሪካ ኤምባሲን ጨምሮ ሌሎች ምዕራባውያን ይህንን ሃሰተኛ መረጃ ከማሰራጨት ባለፈ ዜጎቻቸው ኢትዮጲያን ለቀው እንዲወጡ በተደጋጋሚ ጫና ሲያደርጉ መቆየታቸውን ሃላፊው አንስተዋል ፡፡

ይሁን እንጂ መንግስት የወሰደው የተጠናከረ እርምጃ የሽብር ቡድኑን በማዳከሙ ዛሬ ላይ እነዚህ ቅስቀሳ ሲያደርጉ የነበሩ ኤምባሲዎች ሆነ ሌሎች ተቋማት መደበኛ ስራቸውን ካለምንም የፀጥታ ችግር እያከናወኑ እንደሚገኙ አቶ ከበደ ዴሲሳ በመግለጫቸው አንስተዋል ፡፡

ናትናኤል ሀብታሙ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *