መደበኛ ያልሆነ

ታህሳስ 6፤2014-በአሜሪካ በኮሮና ቫይረስ ህይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር ከ800 ሺ በላይ ሆነ፤ የሟቾቹ ቁጥር ከዋሽንግተን ዲሲ ከተማ ነዋሪዎች ይበልጣል

በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ከፍተኛው ሞት የተመዘገበባት አሜሪካ የሟቾች ቁጥር ከ800 ሺ በላይ ተሻግሯል።እስካሁን በአሜሪካ በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎች ቁጥር 50 ሚሊዮን እየተጠጋ ይገኛል።

ከፍተኛው የሞት መጠን በአሜሪካ የተመዘገበው ባልተከተቡ ሰዎች እና እድሜያቸው በገፉ አዛውንቶች ላይ መሆኑን ሪፖርቶች አመላክተዋል።በንፅፅር ሲቀመጥ የሟቾች ቁጥር ከ2020 ዓመት ይልቅ እየተገባደደ በሚገኘው 2021 ከፍተኛ ሞት ተመዝግቧል።

ባለፉት 11 ሳምንታት ብቻ 100ሺ ሰዎች በአሜሪካ በቫይረሱ ህይወታቸውን ያጡ ሲሆን ቫይረሱ በከፍተኛ ፍጥነት ለሰዎች ህልፈት ምክንያት እየሆነ መምጣቱም ተጠቁሟል። ከ800 ሺ በላይ ሰዎች በቫይረሱ ህይወታቸውን ያጡት ባለፉት 650 ቀናት ውስጥ ነው።

በአሜሪካ በቫይረሰ ህይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር ከዋሽንግተን ዲሲ አልያም ከቦስተን ከተማ ነዋሪዎች ቁጥር የበለጠ ነው።ብራዚል በወረርሽኙ 616ሺ ሞት ሲመዘገብባት በሟቾች ብዛት በሶስተኛ ደረጃ በምትቀመጠው ህንድ ከ475ሺ በላይ ሰዎች በቫይረሱ ህይወታቸውን አጥተዋል።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *