መደበኛ ያልሆነ

ታህሳስ 6፤2014-በደቡብ ወሎ ዓለም አቀፍ የረድኤት ተቋማት እያደረጉት ያለዉ ድጋፍ መሻሻል ማሳየቱ ተገለፀ

በደቡብ ወሎ ዞን ካለዉ ከፍተኛ ቁጥር ተፈናቃይ አንጻር ዓለም አቀፍ የረድኤት ተቋማት እያደረጉት ያለዉ ድጋፍ መሻሻል ማሳየቱን የደቡብ ወሎ ዞን አደጋ መከላከል እና ምግብ ዋስትና ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ መሳይ ማሩ ገልፀዋል። የረድኤት ተቋማቱ ከገንዘብ እስከ አይነት ድጋፎችን ለተፈናቀሉ ወገኖች እያደረሱ እንደሚገኙም ተናግረዋል ።

ከዚህ በፊት ብስራት ራዲዮ በዞኑ ዓለም አቀፍ የረድኤት ተቋማት ተገቢዉን ድጋፍ እያደረጉ እንደማይገኝ መዘገቡይታወሳል።ለተፈናቃዮች በሚደረገው ድጋፍ ተደራሽነት ላይ የተወሰኑ ችግሮች እንዳሉ በመግለፅ ይህንንም ችግር ለመቅረፍ ከአማራ ክልላዊ መንግስት ጋር የመረጃ ልውውጦችን እያደረጉ እንደሚገኝ እና ድጋፉ የሚያስፈልጋቸውን ሰዎች የልየታ ስራዎችን እየተከናወነ እንደሚገኝ ተናግረዋል ።

በተጨማሪም ምግብ ነክ የሆኑ ግብአቶች የምግብ ዘይት እና ጥራጥሬ እንዲሁም ምግብ ነክ ያልሆኑ እንደ ፍራሽ ፣ ብርድ ልብስ ፣ የወለል ምንጣፍ ፣ ለህጻናት እና ለሴቶች የንጽህና መጠበቂያ ድጋፎች እንደሚያስፈልግ አቶ መሳይ ለብስራት ሬድዮ ጨምረው ተናግረዋል።

በረከት ሞገስ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *