መደበኛ ያልሆነ

ታህሳስ 6፤2014-ኤርትራዊው ቢኒያም ግርማይ የአፍሪካ ምርጥ ብስክሌተኛ ተብሎ ተመረጠ

ኤርትራዊው ብስክሌተኛ ቢኒያም ግርማይ በጋቦን በተካሄደው ዓመታዊው የላ ትሮፒካል አሚሳ ቦንጎ በማሸነፍ የአመቱ ምርጥ ብስክሌተኛ ተብሎ ተመርጧል። የ21 ዓመቱ ወጣት ለሁለት ተከታታይ ጊዜ ሽልማቱን ከደቡብ አፍሪካዊው ሪያን ጊብሰን እና ከሀገሩ ልጆች መርሃዊ ቅዱሳን እና ሄኖክ ሙሉብርሃን በመብለጥ አሸንፏል።

በአፍሪካ የብስክሌት ውድድር በሁሉም ምድቦች በግልም ሆነ በቡድን የኤርትራዊያን የበላይነት አለ።ባለፉት አስር ዓመታት ብቻ ስድስት ጊዜ በወንዶች ሻምፒዮን በመሆን ኤርትራ ብልጫ ይዛለች።

በርካታ ኤርትራውያን ፕሮፌሽናል ብስክሌተኞች በአውሮጳ እና በደቡብ አፍሪካ የሚገኙ ክለቦች ስኬታማ ሆነዋል።በ2015 ቱር ደ ፍራንስ ላይ ዳንኤል ተክለሀይማኖት የፖልካ ዶ ማልያን የለበሰብ የመጀመሪያው አፍሪካዊ ነው።

በሚኪያስ ፀጋዬ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *