መደበኛ ያልሆነ

ታህሳስ 6፤2014-የአለም የጤና ድርጅት በደቡብ ሱዳን ሚስጥራዊ በሆነ መልኩ በርካታ ሰዎችን እየገደለ ነው የተባለውን በሽታ ሊያጣራ መሆኑ ተሰማ

በደቡብ ሱዳን ጆንግሌይ ግዛት ፋንጋክ በተባለ አካባቢ እስካሁን ምንነቱ ባልታወቀ ሚስጥራዊ በሽታ 100 የሚጠጉ ሰዎች ህይወታቸው ማለፉን የአለም የጤና ድርጅት አስታውቋል።ባለፈው ሳምንት የሀገሪቱ የጤና ሚኒስቴር ባወጣው መረጃ ምንነቱ ባልታወቀ በሽታ ሰዎች እየሞቱ ይገኛል ሲል መግለፁ ይታወሳል።

በአካባቢው የተሰበሰቡ የመጀመሪያ ናሙናዎች የኮሌራ በሽታ አለመሆኑን ማረጋገጥ ተችሏል።ለችግሩ ፈጣን ምላሽ የሚሰጥ ቡድን በአካባቢው በፍጥነት እንዲላክ መወሰኑን የአለም የጤና ድርጅት ከፍተኛ ባለስልጣን ሺላ ባያ ተናግራለች።

ወደ አካባቢው ለመግባት ካለው የጎርፍ ችግር ጋር በተያያዘ አዳጋች እንደሆነም ተጠቁሟል።የህክምናው ቡድኑ ከጁባ ወደ ስፍራው በሄሊኮፕተር እንደሚጓዝ ይጠበቃል።

በሚኪያስ ፀጋዬ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *