መደበኛ ያልሆነ

ታህሳስ 7፤2014-በቀን ከአንድ መቶ በላይ የተፈናቀሉ ዜጎችን ወደቀያቸው እያደረስኩ ሲል ዘመን ባስ ትራንስፖርት አስታወቀ

ዘመን ባስ ትራንስፖርት ተፈናቅለው በአዲስ አበባ እና በሌሎች ማቆያ ጣብያዎች የሚገኙ እና ወደ ቀዬአቸው ለሚመለሱ ዜጎች ነፃ የትራንስፖርት አገልግሎት መስጠት ከጀመረበት ታህሳስ 4 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ በቀን ከአንድ መቶ በላይ የተፈናቀሉ ዜጎችን ወደ ቀያቸው እያደረሰ መሆኑን አስታውቋል፡፡

ዘመን ባስ ኢትዮጵያ ትራንስፖርት አሸባሪው ህወሃት በከፈተው ጦርነት ምክንያት ከሚኖሩበት አካባቢ ተፈናቅለው አዲስ አበባ እና በተለያዩ ማቆያ ጣቢያዎች ወደ ቀያቸው የመመለስ ስራን መቀጠሉን የዘመን ባስ የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ እይላቸው አያና ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል።

አገልግሎቱን መስጠት ከተጀመረበት ካሳለፍነው ሰኞ አንስቶ ከአዲስ አበባ ደሴ 460 ሰዎችን ከደብረብረሃን ደሴ ደግም ከ150 በላይ ተፈናቃዮችን በነፃ ማድረሱን ተናግረዋል።
የነፃ ትራንስፖርት አገልግሎቱ ለቀጣይ ስድስት ቀናትም እንደሚቀጥልም ገልፀዋል።

በሚሰጠው የሰብአዊ ድጋፍ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን ወደ ቀያቸዉ ለመመለስ መታሰቡን ያነሱ ኃላፊው መነሻቸው ላምበረትና ደብረ ብርሃን ያደረጉ የዘመን አውቶቡሶች መድረሻቸውን ከሸዋሮቢት ጀምሮ እስከ ደሴ ከተማ በማድረግ አገልግሎት እየሰጡ ይገኛል።አቅመ ደካሞች፣ አካል ጉዳተኞች፣ ነፍጡሮችና እና ህጻናት የያዙ ሰዎች ቅድሚያ እየተሰጣቸው እንደሚገኝም ተገልጿል።

በጦርነቱ የተፈናቀሉ ዜጎች አሁንም ላምበረት በሚገኘው የትኬት ቢሮ በአካል በመመዝገብ
ወይም 6162 ላይ በመደወል አገልግሎቱን ማግኘት እንደሚችሉም አቶ እይላቸው አያና ጨምረው ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል።

በትግስት ላቀው

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *