መደበኛ ያልሆነ

ታህሳስ 7፤2014-በቤጂንግ በሚሰናዳው የክረምት ኦሎምፒክ ፑቲን እንደሚገኙ ተናገሩ፤ የአሜሪካና እንግሊዝን ከፍተኛ ባለስልጣናት አንታደምም በሚለው አቋም ፀንተዋል❗️

የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን እ.ኤ.አ. በ 2022 በቤጂንግ በሚካሄደው የክረምት ኦሎምፒክ ላይ ለመገኘት ቃል ገብተዋል ፣ ይህም በውድድሩ ላይ መገኘታቸውን ከገለፁት የዓለም መሪዎች የመጀመሪያ ያደርጋቸዋል።ይህንን አስተያየት ፑቲን የሰጡት ከቻይና ፕሬዝዳንት ዢ ጂንፒንግ ጋር በቪዲዮ በተደረጉት ውይይት ሲሆን በቤጂንግ ለመገኛት በጉጉት እንደሚጠባበቁ ተናግረዋል።

በውድድሩ ላይ የምዕራባውየኑ ሀገራት እንደማይገኙ እየገለፁ ይገኛል።ለዚህም ምክንያቱ ደግሞ በቻይና ተፈጽሟል በተባለው የሰብአዊ መብት ረገጣ ቢሆንም ቤጂንግ ግን ውንጀላውን የሀሰት ስትል ታጣጥለዋለች።

በውይይቱ ፑቲን ከአለም አቀፍ የስፖርት ትብብር ጋር በተያያዘ ሁሌም የምንደጋገፍ መሆናችንን ለመግለፅ እወዳለሁ፤ ስፖርትን ፖለቲካ ለማድረግ የሚደረገውን ጥረት እንቃወማለን ሲሉ ተናግረዋል። የአሜሪካ፣ እንግሊዝ፣ አውስትራሊያ እና ካናዳ ከፍተኛ ባለስልጣናት በየካቲት ወር በሚካሄደው የክረምት ጨዋታዎች ላይ እንደማይገኙ ተናግረዋል። ይሁን እንጂ የእነዚሁ ሀገራት አትሌቶች በውድድሩ ይካፈላሉ።

የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ዋንግ ዌንቢን “ዩናይትድ ስቴትስ፣ ብሪታንያ እና አውስትራሊያ የኦሎምፒክ መድረክን ለፖለቲካ ፍጆታ ተጠቅመዋል” ሲሉ ተናግረዋል። የጃፓኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ፉሚዮ ኪሺዳ በጨዋታው ላይ ለመገኘት እቅድ እንደሌላቸውም ገልፀዋል።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *