መደበኛ ያልሆነ

ታህሳስ 7፤2014-ሶማሊላንድ የቀድሞ የሶማሊያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርን በቁጥጥር ስር አዋለች

የሶማሊያ የቀድሞ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ራሷን ከሶማሊያ የተነጠለች ሀገር ናት ብላ የምታውጀው የሶማሌላንድ ሪፐብሊክ በቁጥጥር ስር አውላለች። መሀመድ ኦማር አርቴ ቃሊብ በሃርጌሳ አየር ማረፊያ በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን ስለታሰሩበት ምክንያት ምንም ዓይነት ማብራሪያ አልተሰጠውም። የቀድሞ ምክትል ጠቅላይ ሚስተር ቃሊብ ላለፉት ጥቂት ወራት በከተማው ውስጥ እንደነበሩ ግን ተነግሯል።

እኚሁ የቀድሞ የሶማሊያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ሶማሊላንድን ነፃነቷን እንዳታገኝ ይቃወሙ ነበር በሚል ይቀርብባቸው የነበረው ክስ ባለፈው ዓመት ጥቅምት ወር ላይ በሶማሊላንድ ፕሬዝዳንት ሙሴ ቢሂ ይቅርታ ተሰጥቷቸዋል። ከሶማሊያ የህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት አባልነት ከለቀቁ በኃላ በሀርጌሳ በህመም ላይ የነበሩትን አባታቸውን ለማስታመም ህይወታቸው ካለ በኃላ የመቅበር እድል አግኝተዋል።

የሶማሊላንድ ፕሬዝዳንት ቢሂ በቅርቡ መንግስት በክልሉ ውስጥ ያሉ ሰዎች በፖለቲካ ውስጥ እንዳይሳተፉ የሚከለክሉ ትእዛዝ ማውጣታቸው የሚታወስ ሲሆን ይህንን የሚደፍሩም ምህረት እንደማይደረግላቸው አስጠንቅቀዋል።

በሚኪያስ ፀጋዬ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *