አሸባሪው እና ወራሪው ህወሓት የኮምቦልቻን ከተማ በወረራ ይዞ በቆየበት ቀናት ዉስጥ በመቶ ሚሊዮን የሚቆጠር ብር በመሰብሰብ ለሀገር ልማት በማዋል የበኩሉን አስተዋጽኦ ሲያደርግ በነበረው የኮምቦልቻ ገቢዎች ቅ/ጽ/ቤት ላይ ከፍተኛ ውድማት ማድረሱ ተገልጿል፡፡
መዳረሻውን ጥፋት አድርጎ ተግባሩን እያሳየ የሚገኘው የሽብር ቡድኑ በጉምሩክ ኮሚሽን የኮምቦልቻ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ሶስት መጋዘን ዉስጥ የነበሩ ንብረቶችን ሙሉ ለሙሉ ከመዝረፉም በላይ የቢሮ መገልገያ ቁሳቁሶችን ማውደሙን የቅ/ጽ/ቤቱ ስራ አስኪያጅ አቶ ሰማን ዳውድ ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል፡፡
የቢሮ መገልገያ ቁሳቁሶችን ከማውደሙም በላይ የግብር ከፋዮችን እና የሰራተኛውን ማህደር እና ሰነድ ከጥቅም ውጭ ቡድኑ አድርጓል፡፡በአሁኑ ሰዓት ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ወደ ቀድሞ ስራ ለመግባት የተለያዩ ስራዎች እያከናወነ እንደሚገኝ እና በቀጣይም የወደሙ ንብረቶችን በዝርዝር እንደሚያሳውቅ የቅ/ጽ/ቤቱ ስራ አስኪያጅ አቶ ሰማን ዳውድ ለጣቢያችን ጨምረዉ ተናግረዋል፡፡
በሳምራዊት ስዩም