መደበኛ ያልሆነ

ታህሳስ 11፤2014-በተሽከርካሪ አካል ውስጥ ተደብቆ ወደ አዲስ አበባ የገባ ከ6 ሺሕ በላይ የክላሽ ጥይት እና የብሬን ዝናር ተያዘ

የአዲስ አበባ ፖሊስ በተሽከርካሪ አካል ውስጥ ተደብቆ ወደ አዲስ አበባ የገባ ከ6 ሺሕ በላይ የክላሽ ጥይት እና የብሬን ዝናር ከብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ጋር በመተባበር መያዙን አስታውቋል፡፡

መነሻውን ባህርዳር ከተማ ያደረገ ላንድ ሮቨር ተሽከርካሪ አካል ውስጥ ተደብቆ ወደ አዲስ አበባ የገባ ብዛቱ 6985 የክላሽ ጥይት እና እያንዳንዱ 492 የብሬን ጥይት መያዝ የሚችል አራት የብሬን ዝናር በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ልዩ ቦታው አዲሱ ገበያ ድል በር አካባቢ ታህሳስ 9 ቀን 2014 ዓ/ም ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ላይ ከብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ጋር በመተባበር እጅ ከፍንጅ እንደተያዘ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

ጥይቱን ሲያዘዋውሩ የተገኙ ሁለት ተጠርጣሪዎች እና ለህገ-ወጥ ተግባር የተገለገሉበት አንድ ተሽከርካሪ በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራው እየተጠራ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ገልፆል፡፡

የከተማዋን ሰላምና ደህንነት ለማደፍረስ የሚንቀሳቀሱ ግለሰቦችን ህገ-ወጥ ተግባር በማጋለጥ ህብረተሰቡ ለፀጥታ አካለት እያደረገ ያለውን ትብብር አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪውን ማስተላለፉን ከአዲስ አበባ ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *