መደበኛ ያልሆነ

ታህሳስ 11፤2014-በጅማ ከተማ ሀሰተኛ ማስረጃን እስከ ስምንት ሺ ብር ሲሸጥ የነበረው ግለሰብ በእስራት ተቀጣ

በጅማ ከተማ መስተዳድር ወረዳ 2 በቾ ቦሬ አካባቢ ነዋሪ የሆነው በላቸው ወልዴ የተባለው ግለስብ በተከራየበት ቤት ውስጥ ሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃን፣መንጃ ፍቃዳ፣ሀሰተኛ የመሬት ካርታ ኣና የወሳኝ ኩነት ማረጋገጫ ሰርተፍኬቶችን በዋጋ ተምኖ ሲሸጥ መቆየቱን የጅማ ከተማ ፖሊስ አስታውቋል።

የጅማ ከተማ ወረዳ 2 የሙስና እና የመንግስት ገቢዎች ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎች መርማሪ ዋና ሳጅን መንበሩ ይተና በተለይ ለብስራት ሬዲዮ እንደተናገሩት ግለሰቡ አንድ ሀሰተኛ ማስረጃን እስከ ስምንት ሺ ብር ሲሸጥ እንደነበር ገልጸዋል።

ግለሰቡ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ማስረጃ ያለው ቢሆንም ከጅማ ዩንቭርስቲ በሲቪል ኢንጂነሪንግ ተምሮ የተመረቀ በማስመሰል ሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃ ማዘጋጀቱ ተገልጿል። በመኖሪያ ቤት ውስጥ 32 ሀሰተኛ የተለያዩ ተቋማት ማህተሞች፣ከ1600 በላይ የተለያዩ ማስረጃዎች መገኘቱን ሳጅን መንበሩ ተናግረዋል፡፡

ፖሊስም የምርመራ መዝገቡን በሰው እና በሰነድ ማስረጃ በማስደገፍ ለጅማ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በማቅረቡ ተከሳሽ በላቸው ወልዴ በአራት አመት እስራት እንዲቀጣ ተወስኖበታል።

በሳምራዊት ስዩም

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *