መደበኛ ያልሆነ

ታህሳስ 11፤2014-በፊሊንፒንስ በሀይለኛ አውሎ ንፋስ የተነሳ የሟቾች ቁጥር 208 መድረሱ ተሰማ

ባሳለፍነው ሀሙስ በፊሊፒንስ የደረሰው ሀይለኛ አውሎ ንፋስ ቢያንስ 208 ሰዎች ህይወታቸውን እንዳጡ ፖሊስ አስታውቋል።ራይ የተሰኘው ይህ አውሎ ንፋስ በሰዓት 195 ኪሜ እንደሚነፍስ ተነግሮለታል።አውሎ ንፋሱ በሀገሪቱ የደበብ ምስራቅ ደሴቶችን ሲመታ ወደ 300ሺ የሚጠጉ ሰዎች እንዲፈናቀሉ ምክንያት ሆኗል።

በአደጋው ህይወታቸውን ካጡ ሰዎች በተጨማሪ ቢያንስ 239 ሰዎች ክፉኛ መጎዳታቸውን የአካባቢው ፖሊስ ያስታወቀ ሲሆን 52 ሰዎች ደግሞ እስካሁን የደረሱበት አልታወቀም። የደረሰውን የጉዳት መጠን ለማረገገጥ አስቸጋሪ ነው የተባለ ሲሆን ለዚህም ምክንያቱ ደግሞ በበርካታ አካባቢዎች የመሰረት ልማት ውድመት በማጋጠሙ የተነሳ ነው።

የመሬት መንሸራተትና የጎርፍ አደጋ አሁንም ስጋት ደቅኗል።ዓለም አቀፍ የቀይ መስቀልና ቀይ ጨረቃ ማህበር የአስቸኳይ ጊዜ የ22 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ድጋፍ እንደሚያስፈልገው ጥሪ አቅርቧል።

ፊሊፒንስ በመሰል አደጋ በ2013 ከስድስት ሺ በላይ ሰዎች ህይወታቸውን ያጡበት ክስተት አጋጥሞ እንደነበር ይታወሳል።

በሚኪያስ ፀጋዬ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *