መደበኛ ያልሆነ

ታህሳስ 11፤2014-ኦሎምፒያ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በማዳበርያ የተጠቀለለ በርካታ ፎርጂድ ዶላር ተገኘ

በቂርቆስ ክፍለከተማ ወረዳ 01 ልዩ ስሙ ኦሎምፒያ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ በማዳበርያ የተጠቀለለ በርካታ ፎርጅድ ዶላር መገኘቱ የክፍለ ከተማው ኮሚኒኬሽን ቢሮ አስታውቋል፡፡

ታህሳስ 9 ቀን 2014 ዓ.ም በክፍለ ከተማው ወረዳ 01 ልዩ ቦታው ኦሎምፒያ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በርካታ የአሜሪካን ፎርጂድ ዶላር በማዳበሪያ መሰል ነገር ተጠቅልሎ መገኘቱን የኮሚኒኬሽ ቢሮ ሀላፊው አቶ አብዱ ሰይድ ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል።

ፎርጂድ ዶላሩ የተገኘው በህብረተሰቡ ጥቆማ መሆኑን የተገለፀ ሲሆን በቀጣይም በየአካባቢው አጠራጣሪ የሆኑ ነገሮችን ህብረተሰቡ ሲመለከት በአቅራቢያው ወደሚገኝ የፖሊስ ተቋም በመሄድ ወይም ለጥቆማ ተብለው በተከፈቱ የስልክ መስመሮች ደውሎ ለፀጥታ ሀይሉ ጥቆማ እንዲጠቁም ጥሪ ቀርባል፡፡

በትግስት ላቀው

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *