
የዓለማችን ባለጸጋ ሰዉ ኤሎን ማስክ በዚህ አመት ብቻ 11 ቢሊየን ዶላር ታክስ እንደሚከፍል በትዊተር ገፁ አስፍሯል።ማስክ ምን ያህል ታክስ እንደሚከፍል በማህበራዊ ሚዲያ ከሰሞኑ ከፍተኛ ዉዝግብና ክርክር ተስተዉሏል፡፡
ቢሊየነሩ ይህንኑተከትሎ በዚህ አመት ከ11 ቢሊዮን ዶላር በላይ ግብር እከፍላለሁ ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡የኤሌትሪክ መኪና አምራች ቴስላ እና የኤሮስፔስ አምራች ስፔስ ኤክስ መስራች ማስክ በተያዘዉ 2021 ዓመት መጀመሪያ የአለማችን ባለጸጋ ሰዉ መሆኑ ይፋ መደረጉ ይታወሳል፡፡
ብሉምበርግ በቢሊየነርስ ዝርዝር መረጃዉ እንደገለጸዉ ከሆነ የማስክ ሀብት 243 ቢሊየን ዶላር እንደሚደርስ ይፋ አድርጓል፡፡ የቴስላ ዋጋ ሀብት ተመን አንድ ትሪሊዮን ዶላር አካባቢ ሲሆን እና የስፔስ ኤክስ ደግሞ 100 ቢሊዮን ዶላር ዋጋ አለዉ፡፡
ባለፈው ሳምንት ማስክ የታይም መጽሔት የአመቱ ምርጥ ሰው ተብለዉ መመረጣቸዉ ይታወሳል፡፡ ዲሞክራቷ ሴናተር ኤልዛቤት ዋረን በትዊተር ገጿ የማስክ የዓመቱ ሰዉ ተብለዉ በታይም መጽሄት መመረጣቸዉን ተከትሎ “የተጭበረበረውን የግብር ኮድ እንለውጥና ‘የአመቱ ምርጥ ሰው’ በእርግጥ ግብር እንዲከፍሉ ይሁን ሲሉ መተቸታቸዉ ይታወሳል፡፡
ማስክ ለሴናተር ዋረን በትዊተር ገፃቸው በሰጡት ምላሽ ፣ “በዚህ አመት በታሪክ ውስጥ ከየትኛውም አሜሪካዊ የበለጠ ግብር እከፍላለሁ” ብለዋል ።
በስምኦን ደረጄ