መደበኛ ያልሆነ

ታህሳስ 12፤2014-ኦሚክሮን የተሰኘዉ ልዉጥ የኮሮና ቫይረስ ኢትዮጵያ ዉስጥ መኖር አለመኖሩ በአስራ አምስት ቀናት ውስጥ ይፋ ይደረጋል ተባለ

በደቡብ አፍሪካ የተገኘዉና ኦሚክሮን የሚል ስያሜ የተሰጠው ልዉጥ የኮሮና ቫይረስ ወደ ኢትዮጲያ መግባት አለመግባቱ በአስራ አምስት ቀናት ውስጥ ይፋ እንደሚደረግ የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

በዓለም ላይ የሚገኙ ከ89 ሀገራት በላይ ኦሚክሮን የተባለው የኮሮና ቫይረስ መከሰቱን ሪፖርት ማድረጋቸውን በጤና ሚኒስቴር የኮቪድ-19 ምላሽ ግብረ ሃይል አስተባባሪ ዶክተር መብራቱ ማሴቦ ለብስራት ሬድዮ የተናገሩ ሲሆን ይህ ቫይረስ በኢትዮጲያ የመከሰት እድሉ ሰፊ መሆኑን አንስተዋል፡፡

ሙሉ በሙሉ አልተከሰተም ብሎ ለመናገር እንደሚያቸግርም የተናገሩት ዶክተር መብራቱ ኦሚክሮን ቫይረስ ከሌሎች የኮሮና ቫይረስ ዓይነቶች አየር ላይ የመቆየት እድለ ሰፊ በመሆኑ በቀላሉ በርካታ ሰዎችን በአንዴ የማጥቃት ባህሪ አለው ብለዋል፡፡በኢትዮጲያ ተከስቷል የሚለውን ግምት ለማረጋገጥ ናሙና እንደተወሰደም ተጠቁሟል፡፡

በኢትዮጲያ በኮሮና ቫይረስ በቀን የሚያዘው የሰው ቁጥር እየጨመረ መሆኑን የተነገረ ሲሆን ያልተከተቡ ሰዎች የመያዝ እድላቸው አሁንም ሰፊ መሆኑንም እና የተከተቡ ሰዎችም በቫይረሱ ቢያዙ እንኳን ህመሙ እንደማይበረታባቸው እና ለሞት እንደማይዳረጉ የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡በዚህ ምክንያትም አሁንም ሰዎች ክትባቱን እንዲከተቡ ጥሪ ቀርባል፡፡

በትግስት ላቀዉ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *