መደበኛ ያልሆነ

ታህሳስ 12፤2014-የኢትዮጵያ የዲያስፖራ አባላት በሀዋሳ ከተማ ምንም አይነት የፀጥታ ችግር አለመኖሩን ተረድተው ከተማዋን እንዲጎበኙ ጥሪ ቀረበ

ሀዋሳ ከተማ ምንም አይነት የፀጥታ ችግር አለመኖሩን በመረዳት ወደሀገር የሚገቡ ዲያስፖራዎች በከተማዋ ያለስጋት ጊዜያቸውን ማሳለፍ እንዲችሉ የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ጥሪ አቅርቧል፡፡ከዚህ ቀደም አንዳንድ የፀጥታ ችግሮች አልፎ አልፎ ሲከሰቱ እንደነበር በማስታወስ ካለፈው አንድ ዓመት ወዲህ ግን ከተማዋ በአስተማማኝ ሰላምና መረጋጋት ላይ እንደምትገኝ የከተማዋ ከንቲባ ረ/ኘሮፌሰር ፀጋዬ ቱኬ ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል፡፡

ሀዋሳ ከተማ በተለይም ለቱሪዝም እና ኮንፍረንስ እጅግ ተመራጭ የሆነች ከተማ መሆናን ያነሱት ከንቲባው የጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ ጥሪን ተቀብለው ወደ አገር ቤት የሚገቡ ዲያስፖራዎች ከተማዋን እንዲጎበኙ ከፍተኛ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ለእንግዶቹ ሰላምና ደኅንነት በከተማዋ ልዩ ቡድን መቋቋሙንም የገለፁ ሲሆን 24 ሰዓት ደኅንነታቸው ተጠብቆ መንቀሳቀስ የሚችሉበት ዝግጅት መደረጉን ረ/ኘሮፌሰር ፀጋዬ ጨምረው ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል፡፡

ሆቴሎች እና የቱሪዝም መዳረሻዎች እንግዶቹን ከተለመደው መንገድ በተጨማሪ በልዩ ሁኔታ እንዲያስተናግዱ ምክክር እየተደረገ መሆኑን ገልፀው ወደ አገር ቤት የሚገቡ ዲያስፖራዎች ከተማዋን እንዲጎበኙም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በትግስት ላቀው

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *