መደበኛ ያልሆነ

ታህሳስ 12፤2014-የዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ፍርድ ቤት በእንግሊዝ ባንክ የተቀመጠውን የቬንዙዌላን ወርቅ መጠቀምን በተመለከተ ፕሬዝዳንት ማዱሮ ያቀረቡትን ጥያቄ ውድቅ አደረገ

የእንግሊዝ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የቬንዙዌላ ፕሬዝዳንት ኒኮላስ ማዱሮ በእንግሊዝ ባንክ ውስጥ የተከማቸ 1.95 ቢሊዮን ዶላር የሚሆን ወርቅ እንዳያገኙ ከልክሏል።ማዱሮ ገንዘቡ በሀገሪቱ ውስጥ ኮቪድ-19ን ለመዋጋት የሚወል ነበር ሲሉ ተናግረዋል።

ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ የቀደመውን የይግባኝ ፍርድ ቤቱን ውሳኔ ሽሯል፡፡ዩናይትድ ኪንግደም እንደ ህጋዊ መሪ የምትቆጥረው የተቃዋሚ መሪ ሁዋን ጌዮዶ ብቻ በቬንዝዌላ ተቀማጭ ወርቅ ላይ የሚሆነውን መወሰን ይችላል ስትል አስታዉቃለች፡፡

ይህ ቢሆንም ግን ፣ በተግባር ደረጃ እንግሊዝ ከማዱሮ አስተዳደር ጋር ግንኙነት አላት፡፡ተቃዋሚዉ ጌዮዶ እና የቬንዝዌላ ፕሬዝዳንት ማዱሮ ሁለት የተለያዩ ገዥዎችን ለቬንዙዌላ ማዕከላዊ ባንክ ሾመዋል።ከ50 በላይ ሀገራት እንደ ህጋዊ ፕሬዝዳንት እውቅና የተሰጣቸው ጌዮዶ ወርቁ በእንግሊዝ ባንክ ዉስጥ ተከማችቶ እንዲቆይ ይፈልጋሉ።

ከ50 በላይ የምዕራባዉያኑ ሀገራትና አጋሮቻቸዉ ለቬንዙዌላ ተቃዋሚ ሀይል የሀገሪቱ ገዢ ነዉ ብለዉ እዉቅና ቢሰጡም በፕሬዚዳንቱ ቤተ መንግስት ውስጥ የሚገኙት ብሎም፣ የሀገሪቱን ወታደራዊ ሀይል እና ፖሊስን የሚቆጣጠሩት ማዱሮ ገንዘቡን እንዲለቀቅላቸው የእንግሊዝ ባንክን ከሰዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *