መደበኛ ያልሆነ

ታህሳስ 13፤2014-በማዳጋስካር አንድ ሚኒስተር የነበሩበት ሄሊኮፕተር ባህር ላይ ቢከሰከስም ሚኒስትሩ ለ12 ሰዓታት በመዋኘት በህይወት መትረፋቸው ተሰማ

የማዳጋስካን መንግስት ሚኒስትር ሄሊኮፕተራቸው በነፍስ አድን ተልዕኮ ላይ በነበረበት ጊዜ ባህር ተከስክሶ ለ12 ሰአታት በመዋኘት በህይወት መትረፋቸውን ተናግረዋል። የተዳከሙት የፖሊስ ሚኒስትር ሰርጌ ገሌ በቃሬዛ ላይ ሆነው ሲያገግሙ እንደተናገሩት “የምሞትበት ጊዜዬ አይደለም” ብለዋል።

በሄሊኮፕተሩ አብረዋቸው ሲጓዙ የነበሩ ሌሎች ሁለት የደህንነት ባለስልጣናትም ከአደጋው ተርፈዋል። በፖሊስ ሚኒስትሩ የተመራው ቡድን በሰሜናዊ ምስራቅ የሀገሪቱ ክፍል የመንገደኞች ጀልባ የሰመጠበትን አካባቢ ሲቃኝ በሄሊኮፕተራቸው ላይ አደጋ ደርሶባቸዋል።

በሰጠመው ጀልባ 39 ሰዎች ህይወታቸውን ያጡ ሲሆን ፕሬዝደንት አንድሪ ራጆኤሊና በትዊተር ገፃቸው ላይ ህይወታቸውን ላጡት ሀዘናቸውን በመግለፅ ለሚኒስትሩ እና ለሌሎች ሁለት መኮንኖች ያላቸውን አድናቆት ገልፀዋል።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *